የሀገርን ምርት መጠቀም በራስ ከመተማመን ባለፈ የሀገርንም ኢኮኖሚ በማሳደግ ረገድ ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት ተገለፀ፡፡
አዲስ አበባ፡ ነሀሴ 26/2017 ዓ.ም (ኢሥኢ) የኢትዮጵያን ይግዙ በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ከሚገኘው የንግድ ሳምንት ኤክስፖ አካል የሆነ የሃገር ውስጥ ንግድ ፓናል ውይይት በግዙፉ የጥራት መንደር ግቢ ውስጥ በኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት አዳራሽ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል፡፡