Skip to main content
emi

ፕሬዝዳንቱ "የኢትዮጵያን ይግዙ" በሚል መሪቃል የተዘጋጀውን የንግድ ሳምንት በይፋ ከፈቱ፡፡

አዲስ አበባ፡ ነሐሴ 24/2017 ዓ.ም (ኢሥኢ) የኤፌዴሪ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ታዬ አፅቀስላሴ በንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አዘጋጅነት "የኢትዮጵያን ይግዙ" በሚል መሪ ቃል ለሁለተኛ ጊዜ የሚካሄደውን ዓመታዊ የንግድ ሳምንት ኤግዚቢሽንና ባዛር በዛሬው ዕለት በይፋ ከፍተዋል፡፡

በመክፈቻ ፕሮግራሙ ላይ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚንስትር ክቡር ካሳሁን ጎፌ /ዶክተር/፣ ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የጥራት መንደር የስራ ኃላፊችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩትን አስመልክቶ የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፍቅረዓብ ማርቆስ ለክቡር ፕሬዝዳንቱና መክፈቻውን ለታደሙ ሁሉ ገለፃ አድርገዋል፡፡

የኢትዮጵያን ይግዙ የንግድ ሳምንት ኢግዚቪሽንና ባዛር ተኪ ምርቶችን የሚያመርቱ እንዲበረታቱና ሀገራዊ አምራች ካምፓኒዎች እንዲስፋፉ አስተዋፅኦ ከማድረጉም ባሻገር ሌሎች አዳዲስ የቢዝነስ ተቋም እንዲፈጠሩ የስራ እድል ፈጠራንና ሙያን በማሳደግ ረገድም ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል፡፡

በዚህ የንግድ ሳምንት ከሚከናወኑ ዋና ዋና ሁነቶች አንዱ በሀገራዊ አጀንዳዎች በተለይም የንግድ ሴክተሩን ለማዘመን ፍትሃዊነትና ተደራሽንነትን ከማሳደግ፣ በወጪ ንግድ ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶችና ተግዳሮቶች እንዲሁም በወጪ፣ የገቢ እና በፋብሪካ ምርቶች የጥራት ቁጥጥር ስራችን ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ኢ-ኮመርስን ተቋማዊ ለማድረግ ጅምር ስራችንን በተመለከቱ አጀንዳዎች ዙሪያ በዘርፉ ከፍተኛ ተመራማሪዎችና ባለሙያዎች ጥናታዊ ፅህፍ ቀርቦ የፓናል ውይይት እንደሚካሄድ በዚህም አዳዲስ ሃሳቦች ልምዶችና የመፍትሄ አቅጣጫዎች የሚመላከቱበት እንደሚሆን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አብዱልሃኪም ሙሉ /ዶክተር/ ኤግዚቢሽኑ ከመጀመሩ በፊት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ መናገራቸው የሚታወስ ነው፡፡

የኢትዮጵያን ይግዙ 2ኛ ዓመት የንግድ ሳምንት ኢግዚቪሽነና ባዛር ከነሀሴ 24-29/2017 ዓ.ም ድረስ በጥራት መንደር ግቢ ውስ የሚካሄድ ሲሆን የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩትም ራሱን እያስተዋወቀ ይገኛል፡፡ በዚህ አጋጣሚ መላው ህብተረሰብ፣ አጋር አካላት፣ የቢዝነስ ተቋማት እና ሸማቾች በንግድ ሳምንቱ ኢግዚቪሽንና ባዛር እንዲሳተፉ፣ እንዲጎበኙና እንዲሸምቱ እንጋብዛለን፡፡