Skip to main content
Please wait...
Image
emi

አስራ ዘጠነኛው የአፍሪካ ሥነ-ልክ ድርጅት /AFRIMETS/ ጠቅላላ ጉባዔ በስኬት ተጠናቀቀ፡፡

አስራ ዘጠነኛው የአፍሪካ ሥነ-ልክ ድርጅት /AFRIMETS/ ጠቅላላ ጉባዔ በስኬት ተጠናቀቀ፡፡

አዲስ አበባ፡ ነሐሴ 2018 ዓ.ም (ኢሥኢ)

በኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት አዘጋጅነት ከሐምሌ 27 እስከ ነሐሴ 01 ቀን 2018 ዓ.ም ለተከታታይ አምስት ቀናት "ሥነ-ልክ ለዲጅታል ሽግግር ተዓማኒ ልኬቶች ለአፍሪካ የወደፊት ዕጣ ፋንታ" በሚል መሪ ሀሳብ በጥራት መንደር ሲካሄድ የቆየው 19ኛው የአፍሪካ ሥነ-ልክ ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ በስኬት ተጠናቋል፡፡

ጉባዔው ሐምሌ 27 እና 28 በተለያዩ የሥነ-ልክ ዘርፎች የተከፋፈሉ የቴክኒክ ኮሚቴዎች ውይይት ማካሄድ የጀመሩበት ሲሆን ሐምሌ 29 ቀን 2018 ደግሞ የኢፌዴሪ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ካሣሁን ጎፌ፣ የአፍሪካ ሥነ-ልክ ድርጅት ፕሬዝዳንት ዶክተር ሄነሪ ኪቤት ሮቲች፣ የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሙሉጌታ ደርበውን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና ከተለያዩ የአፍሪካና ከአፍሪካ ሀገራት ውጭ የተወጣጡ የዘርፉ ተወካዮች በተገኙበት ጠቅላላ ጉባኤው በድምቀት ተከናውኗል፡፡

በመክፈቻው ወቅት ከላይ የተጠቀሱት ሦስቱ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጠቅለል ባለ መልኩ እንዳሉት ሥነ-ልክ ቀጣዩን የአፍሪካ ልማት በጥራት ላይ የተመሰረተ ለማድረግ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ገበያ ስኬታማ ውድድር ማድረግ እንድትችል በጋራ ልማት እና ጥራት ላይ የተመሰረተ ትስስር እንደሚያስፈልግ አብራርተዋል፡፡ አገልግሎቶች ሁሉ ወደ ዲጅታል ስርዓት ባመሩበት በዚህ ወቀት ሥነ-ልክ ወሳኙ የትኩረት ማዕከል መሆን እንዳለበት አፅንኦት ተሰጥተው ተናግረዋል፡፡ ምድረ ቀደምት የሆነችው ኢትዮጵያ ሰርታ ባጠናቀቀችው የጥራት መንደር የተከናወነው ይህ ኹነት ሀገሪቱ በተለያዩ ታላላቅ መድረኮች አሰባሳቢነቷ ተጠናክሮ መቀጠሉን የሚጠቁም የልማት አቅጣጫ ስለመሆኑ አውስተዋል፡፡

በኢትዮጵያ የዘርፉን አገልግሎቶች ዘመኑን በሚመጥን አቅም መገንባት ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ እንደሚገኝ የተብራራ ሲሆን ጉባዔው በአህጉሪቱ የጥራት መሰረተ ልማትን ውጤታማ በሆነ መልኩ እውን ለማድረግ የሚያግዝ መሆኑን ከላይ የተጠቀሱት የሥራ ኃላፊዎቹ ጨምረው ተናግረዋል፡፡

ከ19ኛው የአፍሪካ ሥነ-ልክ ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ጎን ለጎን "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ሀሳብ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሂደዋል፤ በአዲስ አበባ የሚገኙና የተመረጡ ሙዚየሞችንም እንዲጎበኙ ተደርጓል፡፡ 

በመጨረሻም ተሳታፊዎች ለተደረገላቸው መልካም አቀባበልና መስተንግዶ እንዲሁም የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት አፍሪሜትስ የተቋቋመበትን ዓላማ በሚመጥን መልኩ በላቀና ከፍ ባለ ደረጃ ባዘጋጀው ጉባዔ ኩራት እንደተሰማቸው በመግለፅ ምሥጋና አቅርበዋል፡፡

ቀጣዩን የ2027 የአፍሪካ ሥነ-ልክ ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ማለዊ እንድታዘጋጅ ተመርጣለች፡፡

ለተጨማሪ መረጃ

Facebook: http://www.facebook.com/emi.ethiopia 

Website: www.ethiometrology.gov.et

Telegram: https://t.me/Ethiopian_Metrology_Institute 

YouTube: https://www.youtube.com/@EthioMetrology

Email: info@ethiometrology.gov.et