themes/custom/conbiz News | EMI Skip to main content

ኢትዮጵያ ባዘጋጀችው ዓለም አቀፍ የሥርዓተ ምግብ ጉባኤ ላይ የሚሳተፉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተወካዮች የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ፡፡

አዲስ አበባ፡ ሐምሌ 20/2017 ዓ.ም (ኢሥኢ) ኢትዮጵያ ባዘጋጀችው ዓለም አቀፍ የሥርዓተ ምግብ ጉባኤ ላይ የሚታደሙ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተወካዮች የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩትን ጎብኝተዋል።

የኢንስቲትዩቱ አመራርና ሠራተኞች በጉለሌ እፅዋት ማዕከል እንጦጦ ፓርክ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሄዱ።

ዲስ አበባ፡ ሐምሌ 24 ቀን 2017 ዓ.ም (ኢሥኢ) የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት አመራርና ሠራተኞች በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር መሪነት ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመሆን በጉለሌ እፅዋት ማዕከል እንጦጦ ፓርክ በአንድ ጀምበር 700 ሚሊዮን ችግኝ የመትከል መርሐ ግብርን አካሂደዋል።

ኢንስቲትዩቱ በ2017 በጀት ዓመት ከ 94 በመቶ በላይ አፈፃፀም ማስመዝገቡ ተገለፀ፡፡

አዲስ አበባ፡ ሐምሌ 07/2017 (ኢሥኢ) የኢትዮጰያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት አመራርና ሠራተኞች በ2017 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀምና በ2018 ዕቅድ ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል።

የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት ለኢፌዲሪ አየር ሀይል ሲሰጥ የነበረውን ስልጠና አጠናቀቀ፡፡

አዲስ አበባ፡ ሚያዝያ 28/2017 ዓ.ም (ኢሥኢ) የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት ቢሾፍቱ ለሚገኘው የኢፌዲሪ አየር ሀይል ወታደራዊ መኮንኖች ለተከታታይ ሦስት ሳምንታት ሲሰጥ የነበረውን ስልጠና አጠናቅቋል፡፡

በሁሉም ዘርፍ የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡

አዲስ አበባ፡ የካቲት 29/2017 ዓ.ም (ኢስኢ) የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት ሰራተኞች በአለም ለ114ኛ በአገራችን ደግሞ ለ49ኛ ጊዜ "ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል!" በሚል መሪ ቃል ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን /ማርች 8 በዛሬው ዕለት አክብረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት አመራርና ሠራተኞች የዘጠኝ ወር ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ አካሄዱ፡፡

አዲስ አበባ፡ መጋቢት፡ 29/2017 ዓ.ም (ኢሥኢ) የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት አመራርና ሠራተኞች መጋቢት 27 ቀን 2017 ዓ.ም የተቋሙን የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት ዋና ዋና የተግባራት አፈፃፀምን ገምግመዋል፡፡