themes/custom/conbiz News | EMI Skip to main content

የኢንስቲትዩቱ አመራሮችና ሠራተኞች በ2017 በጀት ዕቅድ እና በጊዜ አጠቃቀም ዙሪያ ውይይት አካሄዱ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24/2016 ዓ.ም (ኢስኢ) የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት አመራሮችና ሠራተኞች በ2017 በጀት ዕቅድ፣ በጊዜ አጠቃቀም፣ መልካም ሥነ-ምግባር እና ለጥናትና ምርምር የተቋሙን ነባራዊ ሁኔታ በማስመልከት በአዳማ ከተማ ውይይት አድርገዋል፤የአዳማ ጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪንም ጉብኝተዋል፡፡

የሀገር ውስጥ የህክምና ግብዓት ምርትና የኢኖቬሽን አውደ ርዕይ በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ነው፡፡

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20/2016 ዓ.ም (ኢስኢ) የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ከአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት እና ከሀገር ውስጥ የህክምና ግብዓት አምራች ማህበራት ጋር በመተባበር ከሰኔ 15-20/2016 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ አውደርዕይ በሚሊኒየም አዳራሽ እያካሄደ ይገኛል፡፡

ኢንስቲትዩቱ “ለተሻለ ነገ ዛሬ እንለካለን” በሚል መሪ ቃል ዓለም አቀፉን የሥነ-ልክ ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች አከበረ፡፡

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2016 ዓ.ም (ኢስኢ) የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት አመራሮችና ሠራተኞች ዓለም አቀፉን የሥነ-ልክ ቀን “ለተሻለ ነገ ዛሬ እንለካለን” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ዝግጅቶች አክብረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት ሠራተኞች የዘጠኝ ወር የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ አካሄዱ፡፡

የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት አመራሮችና ሠራተኞች የተቋሙን የ2016 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወር የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ አካሂደዋል፡፡

በቂ ክህሎትና መልካም ስነ-ምግባር ያለው ባለሙያ ለማፍራት የተቋም ባህልና የሠራተኞች ባህሪ ግንባታ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሆነ ተጠቆመ፡፡

አዲስ አበባ፡ ሚያዝያ 07/2016 ዓ.ም /ኢስኢ/ በስነ-ምግባራዊ አመራር፣ በካሊብሬሽን አገልግሎት አሰጣጥ፣ በትራንስፖርት ስምሪት መመሪያ እንዲሁም በስነ-ምግባር ኮድ መመሪያ ዙሪያ የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት የሥራ ኃላፊዎች የተሳተፉበት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በአዳማ ከተማ ተካሂዷል፡፡

የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት ሠራተኞች 13ኛውን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ምስረታ በዓል አከበሩ፡፡

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27/2016 ዓ.ም (ኢስኢ) የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት አመራሮችና ሠራተኞች በህብረት ችለናል! በሚል መሪ ቃል 13ኛውን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ምስረታ በዓል በፓናል ውይይት አክብረዋል፡፡