የተቋሙ የማኔጅመንት አባላት በ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ተወያዩ፡፡
የተቋሙ የማኔጅመንት አባላት በ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ተወያዩ፡፡
አዲስ አበባ፡ ሰኔ 07/2018 ዓ.ም ኢሥኢ
የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት ማኔጅመንት አባላት በ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡
ዕቅዱን ያቀረቡት የኢንስቲትዩቱ የስራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈtፃሚ ወይዘሮ ስንታየሁ ወንድሙ ሲሆኑ የተቋሙን ተልዕኮ መሰረት በማድረግ ከአስር ዓመቱ የስትራቴጂክ ዕቅድ የተቀዳና የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀምን ዋቢ ያደረገ ዕቅድ መዘጋጀቱ ተብራርቷል፡፡ ከዚህ አኳያም ከዋና ዋና ግቦች በመነሳት የሁሉም የስራ ክፍሎች ዝርዝር ተግባራት በጥልቀት ተገምግመዋል፡፡
በ2019 በጀት ዓመት የድጂታል አሰራርን በማጠናከር የተገልጋዮችን እርካታ ከፍ ማድረግ፣ ጊዜው የሚፈልገውን ዘመናዊ አሰራርና ተቋሙን የሚመጥን ብቃት ያለው የሰው ሃይል መፍጠር፣ የክሊብሬሽን አገልግሎቶችን ማስፋት፣ የጥናትና ምርምር ስራዎችን ማካሄድና በወቅቱ ማጠናቀቅ እንዲሁም የጥገና እና መሰል ሥራዎችን በትኩረት ለመፈፀም ጥረት የሚደረግበት ዓመት እንደሚሆን በውይይቱ ላይ አቋም ተወስዷል፡፡
የዕቅድ ውይይቱን የመሩት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ሙሉጌታ ደርበውን (ዶ/ር) ጨምሮ ም/ዋና ዳይሬክተርና ሁሉም የማኔጅመንት አባላት ተሳትፈዋል፡፡ ዶክተር ሙሉጌታ ውይይቱን ሲያጠቃልሉ እንደተናገሩት በእየስራ ክፍሉ የተቀመጡ ግቦችን ቆጥሮ መያዝ በባለፈው በጀት ዓመት የታዩ ክፍተቶችን በመድፈን ከወዲሁ ጠንክሮ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡
የተቋሙን ራዕይና ተልዕኮ ለማሳካት እንደተለመደው በአንድነት ተባብሮና ተከባብሮ መስራት ሲቻል መሆኑን በመገንዘብ ለኢንስቲትዩቱም ሆነ ለሀገር የሚጠቅም ተጨባጭ ውጤት ለማምጣት የማኔጅመንት አባሉ ድርሻ የላቀ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ስለዚህም ስራ ጠንቅቆ በማወቅና በመምራት ለሀገር የሚኖረንን አበርክቶ ማላቅ ይኖርብናል ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡
እንደ ዋና ዳይሬክተሩ ገለፃ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርምን በተመለከተ በዚህ ዓመት በተቋቋመው ኮሚቴ የግንዛቤ ማስጨበጫ በመስጠት፣ በሰንድ፣ በመዋቅር ዝግጅት፣ በሙያ ምድብ፣ በብቃት ማዕቀፍ ዝግጅትና መሰል ጠንካራ ስራዎችን በብቃት በመከወናችሁ ምስጋና ይገባችኋል ያሉ ሲሆን ይህ ጥረት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
Facebook: http://www.facebook.com/emi.ethiopia
Website: www.ethiometrology.gov.et
Telegram: https://t.me/Ethiopian_Metrology_Institute
YouTube: https://www.youtube.com/@EthioMetrology
Email: info@ethiometrology.gov.et