የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት የሥራ ጉብኝት አደረጉ፡፡
ጉብኝቱ ያተኮረው በኢንስቲትዩቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀምና እየተገነቡ የሚገኙ ህንፃዎች ያሉበትን ደረጃ መገምገም ነው፡፡
የቋሚ ኮሚቴው አባላት የሕንፃዎቹን ግንባታ ከተመለከቱ በኋላ በሰጡት አስተያዬት የግንባታ ሂደቱ መልካም ቢሆንም በዓለም ባንክ የተገዙ ግዙፍና ውድ ማሽኖች በቦታ ጥበት ምክንያት ያለሥራ ታሽገው ስለሚገኙ እነሱን ከብልሽት ለማዳንና ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጡ ከዚህ የበለጠ ትኩረት በመስጠት ግናባታው በአጭር ጊዜ የሚጠናቀቅበትን ሁኔታ ማመቻቸት ይጠበቅባችኋል ብለዋል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሙሉጌታ ደርበው በበኩላቸው እንዳሉት የቋሚ ኮሚቴው ግምገማ ትክክል እንደሆነ ጠቅሰው ግንባታውን በትኩረት እየተከታተሉ መሆኑንና በውድ ዋጋ የተገዙ መሳሪያዎችን ፈጥኖ ወደ ሥራ ለማስገባት የሚቻለውን ሁሉ ጥረት እንደሚደርጉ ተናግረዋል፡፡
በጉብኝቱ ወቅት የኢንስቲትዩቱን ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፍቅረአብ ማርቆስን ጨምሮ የዳይሬክቶሬት ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡