የኢፊዲሪ ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አካሄዱ፡፡
አዲስ አበባ፣ ሀምሌ 25/2015 ዓ.ም (ኢስኢ) የኢፊዲሪ ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አካሂደዋል፡፡
በፕሮግራሙ ላይ የኢፊዲሪ ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ ገብረመስቀል ጫላ እና ሚኒስትር ዴኤታዎችን ጨምሮ በኢፌዴሪ ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በጥራት መሰረተ ልማት አስተባባሪነት አራቱ ተጠሪ ተቋማት ማለትም የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት፣ የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት፣ የኢትዮጵያ ተስማሚነትና ምዘና ድርጅት እና የኢትዮጵያ አክሪዲቴሽን አገልግሎት አመራሮችና ሠራተኞች በጋራ በመሆን ሰበታ ዙሪያ ተፍኪ በሚባል አካባቢ በመገኘት አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል፡፡
ከዚህ በፊት በአገር አቀፍ ደረጃ ሀምሌ 10 ቀን 2015 ዓ.ም "ነገን ዛሬ እንትከል" በሚል መሪቃል በአንድ ጀንበር 500 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል በተሰጠው መመሪያ መሰረት ቂሊንጦ በሚገኘው ኢንዱስትሪ ፓርክ ግቢ ውስጥ የችግኝ ተከላ ማካሄዳችን የሚታወስ ነው፡፡