Skip to main content
EMI

ኢትዮጵያ ባዘጋጀችው ዓለም አቀፍ የሥርዓተ ምግብ ጉባኤ ላይ የሚሳተፉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተወካዮች የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ፡፡

አዲስ አበባ፡ ሐምሌ 20/2017 ዓ.ም (ኢሥኢ)

ኢትዮጵያ ባዘጋጀችው ዓለም አቀፍ የሥርዓተ ምግብ ጉባኤ ላይ የሚታደሙ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተወካዮች የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩትን ጎብኝተዋል። የጉብኝቱን ተሳታፊዎች የተቀበሉትና የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሙሉጌታ ደርበው እንደተናገሩት መንግስት በሰጠው ልዩ ትኩረት በምድረ ግቢው ግዙፍ ግንባታዎች መከናወናቸውን ገልፀው ከግንባታዎቹ መካከል ስድቱ ደግሞ በኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት ሥር እንደሚተዳደሩና ብዛት ያላቸው ላቦራቶሪዎችን በውስጣቸው ያቀፉ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

በተጨማሪም ጎብኚዎቹ ካላቸው አጭር ጊዜ እንዲሁም ዓላማቸው ከሆነው የሥርዓተ ምግብ ጉዳይ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸውን ላቦራቶሪዎችን እንዲጎበኙ የጋበዟቸው ሲሆን በየክፍሉ የተመደቡ ባለሙያዎችም አገልግሎቶቻቸው ምን ምን እንደሆኑና ከሥርዓተ ምግብ ጋር ስላላቸው ግንኙነት ገለፃ አድርገዋል፡፡

የጥራት መንደርን በተመለከተ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ የሆኑት ክቡር አቶ እንዳለው መኮንን አጠቃላይ ገለፃ አድርገዋል፡፡

Add new comment

Restricted HTML

  • You can align images (data-align="center"), but also videos, blockquotes, and so on.
  • You can caption images (data-caption="Text"), but also videos, blockquotes, and so on.