Skip to main content
Please wait...
Image
Afar

የከረምት በጎፈቃድ አገልግሎት ሥራ በአፉር ሰመራ ተካሄደ።

የከረምት በጎፈቃድ አገልግሎት ሥራ በአፉር ሰመራ ተካሄደ። 

ኢሥኢ መስከረም 5 /2019 ዓ.ም ሰመራ

የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት አካል የሆኑትና የችግረኞች ቤት የሚገንባበትን መሠረት ድንጋይ የመጣል እና ለተማሪዎች የትምህርት ግብዓቶች ማለትም ቦርሰ፣ ደብተርና ስክሪፕቶ በስጦታ የማበርከት ተግባራት ተከናውነዋል።

በወቅቱም የሰመራ ከተማ ከንቲባ ኢንጂነር አህመድ ኑርሳሊም እንዲሁም የአፉር ክልላዊ መንግሥት ንግድ ቢሮ ዋና እና ምክትል ኃላፊዎች፣ የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፍቅረአብ ማርቆስና የሥራ ክፍሎች ኃላፊዎች እንዲሁም የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ልማት ድርጅት ምክትል ስራአስፈፃሚ ቅድስት ስጦታውና ሌሎች ኃላፊዎቻቸው የተገኙ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን ያቀረቡት ከንቲባ አህመድ እንዳሉት አለኝታችሁን ለማሳየትና መልካም ስጦታችሁን ለማበርከት ሙቀቱን ጭምር ተቋቁማችሁ በመገኘታችሁ ክብር ይሰማናል በቀጣይም አብረን እንደምንሰራ መተማመኔ ከፍ ያለ ነው ብለዋል። 

የንግድና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር ተጠሪ የሆኑት የሁለቱ ተቋማት ኃላፊዎች አቶ ፍቅረአብ ማርቆስና ቅድስት ስጦታው  ጠቅለል ባለ መልኩ እንዳሉት የሰው ልጆች ሁሉ እናትና መገኛ ወደሆነችው አፉር በመምጣታችን ክብርም፣ ኩራትም ሆነ ደስታ ይሰማናል። በቂነው በማለት ሳይሆን አቅማችን በፈቀደ አሥር ቤቶችን ለመገንባትና የሁለት መቶ ተማሪዎችን ቦርሳ፣ ደብተርና ስክሪፕቶ ለመሸፈን በመቻላችን በጣም በጥቂቱም ቢሆን ጫናዎቻችሁን እንደተጋራን ይሰማናል። በቀጣይም እንደ አንድ ቤተሰብነታችን እጅ ለእጅ ተያይዘንና ተደጋግፈን የማንወጣው ችግር የለም ብለዋል።

ለተጨማሪ መረጃ

Facebook: http://www.facebook.com/emi.ethiopia 

Website: www.ethiometrology.gov.et

Telegram: https://t.me/Ethiopian_Metrology_Institute 

YouTube: https://www.youtube.com/@EthioMetrology