themes/custom/conbiz የኢንስቲትዩቱ አመራርና ሠራተኞች በጉለሌ እፅዋት ማዕከል እንጦጦ ፓርክ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሄዱ። | EMI Skip to main content
emi

የኢንስቲትዩቱ አመራርና ሠራተኞች በጉለሌ እፅዋት ማዕከል እንጦጦ ፓርክ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሄዱ።

አዲስ አበባ፡ ሐምሌ 24 ቀን 2017 ዓ.ም (ኢሥኢ)

የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት አመራርና ሠራተኞች በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር መሪነት ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመሆን በጉለሌ እፅዋት ማዕከል እንጦጦ ፓርክ በአንድ ጀምበር 700 ሚሊዮን ችግኝ የመትከል መርሐ ግብርን አካሂደዋል።

በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብሩ ላይ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታዎችና ሠራተኞች፣ የተጠሪ ተቋማት አመራርና ሠራተኞች እንዲሁም የኢትዮጰያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሙሉጌታ ደርበው፣ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፍቅረዓብ ማርቆስን ጨምሮ ሌሎች የተቋሙ አመራርና ሠራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል።

የአረንጓዴ አሻራ በተደራጀ ህዝባዊ ዘመቻ ተግባራዊ መደረጉ በኢትዮጵያ የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ፣ ዘላቂ የመሬት አያያዝና አጠቃቀምን ለማሻሻል ብሎም አስፈሪ እየሆነ የመጣውን የአየር ንብረት ለውጥ ችግር ለመቅረፍ ጠቀሜታው የጎላ ነው ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ደ/ር) የዘንድሮውን የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር "በመትከል ማንሰራራት!" በሚል መሪ ሀሳብ ሰኔ 20 ቀን 2017 ዓ.ም በይፋ ካስጀመሩ በኋላ ኢንስቲትዩቱ የዛሬውን ጨምሮ ለ2ኛ ጊዜ አረንጓዴ አሻራውን አሳርፏል።