themes/custom/conbiz ኢንስቲትዩቱ በ2017 በጀት ዓመት ከ 94 በመቶ በላይ አፈፃፀም ማስመዝገቡ ተገለፀ፡፡ | EMI Skip to main content
emi

ኢንስቲትዩቱ በ2017 በጀት ዓመት ከ 94 በመቶ በላይ አፈፃፀም ማስመዝገቡ ተገለፀ፡፡

ኢንስቲትዩቱ በ2017 በጀት ዓመት ከ 94 በመቶ በላይ አፈፃፀም ማስመዝገቡ ተገለፀ፡፡

አዲስ አበባ፡ ሐምሌ 07/2017 (ኢሥኢ)

የኢትዮጰያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት አመራርና ሠራተኞች በ2017 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀምና በ2018 ዕቅድ ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል። ሪፖርቱን ያቀረቡት የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፍቅረአብ ማርቆስ እንዳብራሩት ባለፈው በጀት ዓመት አዲስ ቢሮ ከመቀየር ጋር ተያይዞ ከባድና ፈርጀ ብዙ ተግባራት የጋጠሙን ቢሆንም ዋና ዋና ተግባራትን ሳንረሳ ጎን ለጎን ማስኬድ በመቻላችን አጠቃላይ የኢንስቲትዩቱን አፈፃፀም ከ94 በመቶ በላይ ማሳካት መቻሉን አስረድተዋል።

ይህን ስኬት ማስመዝገብ የተቻለው ደግሞ ከታች እስከ ላይ ያለው አመራርና ሠራኛ ከፍተኛ የሆነ ቅንጅታዊ አሰራርን በመተግበራቸው ነው፡፡ ይህ ልምድ በቀጣዩ በጀት ዓመትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና ከዚህ የተሻለ ውጤት እንሚመዘገብ እምነቴ የፀና ነው ብለዋል፡፡

እንደ አቶ ፍቅረአብ ገለፃ በጥናትና ምርምር፣ የካሊብሬሽን፣ የጥገና፣ የቴክኒክ ድጋፍና የምክር እንዲሁም የብቃት ማረጋገጥ አገልግሎቶችን በመስጠት ረገድ አመርቂ ስራ ተሰርቷል። ዓለም አቀፍ የእርከን ተዋረድ ትስስር ከመጠበቅና ከማሰራጨት አኳያ ብሎም ከዓለም አቀፍ አቻ የሥነ-ልክ ተቋማት ጋር መልካም የቅንጅት ስራ መከናወኑን ጨምረው ያስረዱ ሲሆን በሌሎች የማህበራዊና በጎ አድራጎት ስራዎች ላይም ተሳትፎ መደረጉን ጠቁመዋል።በዚህ በጀት ዓመት ከ2 መቶ 24 ሚሊዮን ብር በላይ ስራ ላይ በማዋል የተመደበውን በጀት በአግባቡ የተጠቀምን ሲሆን የተፈቀደው በጀት በኢንስቲትዩቱ ታሪክ ከፍተኛው ነው ያሉት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ይህ የሚያመላክተው ደግሞ መንግስት ተቋሙ ለሀገር ያለውን አበርክቶ በውል የተገነዘበ ከመሆኑም ባሻገር የሀገሪቱንም የኢኮኖሚ አቅም እየጎለበተ መሄድ የሚያሳይ ነው ብለዋል።

በሌላ በኩል የተቋሙ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ስንታየሁ ወንድሙ የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድን በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን በቀረበው ዕቅድ ላይ ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጓል፤ የተለያዩ የማሻሻያ ሀሳቦችም ተሰጥቶበታል።

ውይየቱን ያጠቃለሉትና የስራ መመሪያ የሰጡት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሙሉጌታ ደርበው እንደተናገሩት በባለፈው በጀት ዓመት ሁሉም ሠራተኛ ከተሰጠው ዋና ተግባር ባሻገር ሌሎች ተጨማሪ ሥራዎችን በቅንነትና በባለቤትነት ስሜት መከወን በመቻሉ አስደናቂ አፈፃፀም ማስመዝገብ ተችሏል። ለውጤቱ መገኘት የሁሉም ሠራተኛ አስተዋጽኦ የማይተካ ሚና ቢኖረውም ከዚህ ውስጥ ደግሞ ጉልህ ድርሻ የነበራቸውን ሠራተኞች መለየትና ዕውቅና መስጠት በመቻላችንና በሌሎች ላይ የተነሳሽነት ስሜት መፈጠሩ ለውጤቱ መገኘት እንደምክንያት ሊጠቀስ የሚችል ጉዳይ ነው ብለዋል።

ይህ አሰራር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ በ2018 በጀት ዓመት የተቋሙን ራዕይና ተልዕኮ ለማሳካት ሁሉም በቁርጠኝነት መረባረብ እንዳለበት በአፅንኦት አስገንዝበዋል።

Add new comment

Restricted HTML

  • You can align images (data-align="center"), but also videos, blockquotes, and so on.
  • You can caption images (data-caption="Text"), but also videos, blockquotes, and so on.