ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ ዛሬ ብሔራዊ የጥራት መንደርን መረቁ::
በአፍሪከ ደረጃ በአይነቱና በሚሰጠው አገልግሎት ልዩ የሆነና የተለያዩ የጥራት መሠረተ ልማቶችን አንድ አካቶ የያዘው ብሔራዊጥራት በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በይፋ ተመርቋል።
ይህ እጅግ ዘመናዊ የጥራት መንደር ከ8 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ መዋእለ ንዋይ ተመድቦ የተገነባ ሲሆን ከ7 ነጥብ 2 ሄክታር በላይ ቦታ ላይ ያረፈና ከግዙፍ የመንግሥት ፕሮጀክቶች መካከል የሚጠቀስ ነው።
የጥራት መንደሩ በውስጡ እጅግ ዘመናዊ ፋሲሊቲዎች ያሟላ፣ እጅግ የዘመኑ ቤተሙከራዎች ያሉት የምርትና አገልግሎት ጥራት ማረጋገጫ ልቀት ማዕከል ነው።
በጥራት መንደሩ ቅጥር ግቢ በዉጭ ተገልጋዮች እና ለውስጥ ሠራተኞች በቂ የመኪና ማቆሚያ ስፍራዎች ያሉት ነው። ለአይን የሚያምር፣ የአገልግሎት ተጠቃሚዎችና የውስጥ ሠራተኞችን መንፈስ የሚያድስ ከ1 ነጥብ 3 ሄክታር በላይ ቦታ የአረንጓዴ ስፍራም አለው። አረንጓዴ ሥፍራዎችና ምቹ የሥራ አካባቢዎች በሠራተኞችና ለኢንዱስትሪ ምርታማነት የላቀ አስተዋጽኦ እንዳላቸው በሳይንስ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶር ዐቢይ አህመድ አበክረው እንደሚናገሩ ይታወቃል።
ዛሬ በይፋ የተመረቀው ብሔራዊ የጥራት መንደርም በእሳቸው ሃሳብ አመንጪነትና ጥብቅ ክትትል እንዲሁም በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ጠንካራ አመራር እና በጥራት መንደሩ አመራሮችና ሠራተኞች የጋራ ጥረት ሥራው ተጠናቆ ተመርቋል።
የጥራት መንደሩ ወጪና ገቢ ምርቶችንና አገልግሎቶችን ጥራትና ተስማሚነት የሚያረጋግጥ የአፍሪካ የጥራት ልቀት ማዕከል ሊሆን የሚችል ነው።
የሀገራችንን ሁለንተናዊ ዕድገትና የብልጽግና ጉዟችንን የሚያፋጥን የአንድ ማዕከል አገልግሎት መንደር መሆኑ የጉብኝቱ ተሣታፊዎችም መሥክሯል። በክልሎችም ደረጃ ም ይህንን ልምድና ተሞክሮ በመውሰድ የአገልግሎት ተደራሽነትን ለማስፋት እና ከሀገራችን ፈጣን ዕድገት ጋር በትይዩ ለጥራት ተቋማት ግንባታ ትኩረት መስጠት አለባቸው።