themes/custom/conbiz "የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ" በሚል መሪ ቃል የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ተካሄደ፡፡ | EMI Skip to main content
Plantation

"የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ" በሚል መሪ ቃል የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ተካሄደ፡፡

ነሐሴ 17-2016 ዓ.ም ኢስኢ

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮችና ሠራተኞች "የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ" በሚል መሪ ቃል በዛሬው ዕለት እንጦጦ ፓርክ አካባቢ በመገኘት አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዶክተር ከሣሁን ጎፌ ችግኝ ተከላውን ሲያስጀምሩ እንደተናገሩት መንግስት በአንድ ጀምበር 6 መቶ ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል ያስቀመጠውን አቅጣጫ አክብረው በቦታው ለተገኙና አሻራቸውን ላኖሩ ተሳታፊዎች ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በችግኝ ተከላው ላይ ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት ዋና እና ምክትል ዳይሬክተሮች ዶክተር ሙሉጌታ ደርበውና አቶ ፍቅረአብ ማርቆስን ጨምሮ ሌሎች የተቋሙ የስራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡