Skip to main content
Please wait...
Image
emi

ኢንስቲትዩ በከፍተኛ (Primary) ዘዴ የፒኤች (pH) ልኬትን በማረጋገጥ በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የተረጋገጠ መደበኛ ናሙና (CRM) አዘጋጀ፡፡

ኢንስቲትዩ በከፍተኛ (Primary) ዘዴ የፒኤች (pH) ልኬትን በማረጋገጥ በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የተረጋገጠ መደበኛ ናሙና (CRM) አዘጋጀ፡፡

አዲስ አበባ፡ መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ. ኢሥኢ

በኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት የኬሚካል ሥነ-ልክ ምርምር ክፍል በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለውን የሀርነድ ሴል ሲስተም (Harned Cell System) በመጠቀም በ 25 ዲግሪ ሴንቲግሬድ የሙቀት መጠን የ pH = 6.86 ባፈር ሶሉሽንን በከፍተኛ /መሰረታዊ ዘዴ (Primary Method Realization) በስኬት ማረጋገጥ መቻሉን የሥራ ክፍሉ መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ፀደቀ ብርሃኑ አብስረዋል።

እንደ መሪ ሥራ አስፈፃሚው ገለፃ ይህ አገራዊ ስኬት እንደ አሜሪካው NIST እና ሌሎች የዓለም አቀፍ ሥነ-ልክ ተቋማት (NMIs) ሁሉ፣ በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው የፒኤች (pH) የተረጋገጠ መደበኛ ናሙና (CRM) በሀገር ውስጥ ለማዘጋጀት ያስቻለ ታላቅ እርምጃ መሆኑን አስረድተዋል። 

አቶ ፀደቀ አክለውም የተመዘገበው ስኬት በተለይ ለላብራቶሪዎችና ለህብረተሰቡ ጥራቱ የተረጋገጠ የ pH CRM በሀገር ውስጥ ማግኘት ማስቻሉ፣ ያልተረጋገጡ መለኪያዎችን በመጠቀም የሚፈጠሩ የጤና እና የጥራት ስጋቶችን በማስወገድ፣ በመድኃኒት፣ በግብርና፣ በውሃ ጥራትና በምግብ ኢንዱስትሪዎች የሚደረጉ ምርመራዎችን ሙሉ በሙሉ አስተማማኝ በማድረግ! በተጨማሪም የዉጭ ምንዛሬን በማስቀረት ረገድ ፋይዳው የጎላ መሆኑን ያስገነዘቡ ሲሆን በቀጣይም በ pH = 4.01 እና pH =10.01 ለማምረት በትጋት እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

ለተጨማሪ መረጃ

Facebook: http://www.facebook.com/emi.ethiopia 

Website: www.ethiometrology.gov.et

Telegram: https://t.me/Ethiopian_Metrology_Institute 

Youtube: http://www.youtube.com/@EthioMetrology