themes/custom/conbiz የኢትዮጵያን ምርትና አገልግሎት መግዛት ዕድገትን ለማፋጠን ያግዛል ተባለ፡፡ | EMI Skip to main content
dpm

የኢትዮጵያን ምርትና አገልግሎት መግዛት ዕድገትን ለማፋጠን ያግዛል ተባለ፡፡

አዲስ አበባ፡ ነሐሴ 19/2016 ዓ.ም /የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት

የኢትዮጵያን ምርትና አገልግሎት መግዛት የውጭ ምንዛሬን ከማዳን ባሻገር የግሉን የንግድ ዘርፍ ያበረታታል፣ የሀገርንም ዕድገት ያፋጥናል ሲሉ "የኢትዮጵያን ይግዙ" በሚል መሪ ቃል በተከፈተው የንግድ ሳምንት ኤግዚቢሽንና ባዛር መክፈቻ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ ተናግረዋል።

አንደ አቶ አደም ፋራህ ገለፃ የኢትዮጵያ የወጪ ንግድ ማሳያ ማዕከል መቋቋሙ የወጪ ንግድ ሥርዓታችን መልክ በማስያዝና የተቀላጠፈ አሰራር በመዘርጋት ረገድ የጎላ ሚና ይጫወታል ብለዋል፡፡

ከነሐሴ 19 – 23/2016 ዓ.ም በሚቆየው የንግድ ሳምንት ኤግዚቢሽንና ባዛር መክፈቻ ፕሮግራም ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክቡር አቶ አገኘሁ ተሻገር ፣ ሚኒስትሮች: የተጠሪ ተቋማት አመራሮች፣ አምባሳደሮች እና የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ተገኘተዋል፡፡

የኢትዮጵጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩትም የሚያከናውናቸውን ተግባራት በተግባር አስደግፎ ለጎብኝዎች ራሱን አስተዋውቋል፤ በቀጣይ ቀናትም አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡