Skip to main content
Please wait...
Image
emi

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት አመራሮች የህብር ቀንን ምክንያት በማድረግ በመቄዶኒያ ተገኝተው የምሳ ማብላት ፕሮግራም አካሄዱ፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት አመራሮች የህብር ቀንን ምክንያት በማድረግ በመቄዶኒያ ተገኝተው የምሳ ማብላት ፕሮግራም አካሄዱ፡፡

አዲስ አበባ፡ ጳጉሜ 04 ቀን 2018 ዓ.ም ኢሥኢ

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት አመራሮች ጳጉሜ 04 ቀን 2018 ዓ.ም  የሚከበረውን የህብር ቀን ምክንያት በማድረግ በመቄዶኒያ በመገኘት 9 ሺህ ለሚጠጉ አረጋዊያን የምሳ ማብላት ፕሮግራም አካሂደዋል፡፡

ድጋፉን በማስመልከት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማትን በመወከል ንግግር ያደረጉት የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ደስታው መኳንንት እንደተናገሩት ሚኒስቴር መስሪያቤቱና ተጠሪ ተቋማት ጳጉሜ አራትን የመቄዶኒያ ቀን ብለው በሰየሙት መሰረት ዘንድሮም ለሁለተኛ ጊዜ በጋራ እያከበርን እንገኛለን ያሉ ሲሆን ከዚህ ግዙፍና ማህበራዊ ኃለፊነቱትን ከሚወጣ ተቋም ጋር ቀኑን ስናከብር የላቀ ኩራትና ደስታ የሰማናል ብለዋል፡፡ አያይዘውም ይህ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አውስተው የመቄዶኒያ መስራችና ስራ አስኪያጅ የሆኑትን የክብር ዶክተር ቢኒያም በለጠ ለሚያከናውኑት ከባድ ማህበራዊ አገልግሎት የላቀ ምሥጋና አቅርበዋል፡፡

የመቄዶኒያ መስራችና ሥራ አስኪያጅ የክብር ዶክተር ቢኒያም በለጠ በበኩላቸው ቀኑን በመቄዶኒያ ሰይማችሁ በየዓመቱ ለምታደርጉልን ድጋፍ ምስጋና አቀርባለሁ ያሉ ሲሆን ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን እምነት ገልፀዋል፡፡

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት ጳጉሜ 04 የህብር ቀንና አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ በተቋሙ ለሚገኙ አነስተኛ ገቢ ላላቸው 86 ሠራተኞች የዘይትና ዱቄት ስጦታ በማበርከት በምስጋና እና በአብሮነት ዕለቱን አሳልፏል፡፡

Facebook: http://www.facebook.com/emi.ethiopia 

Website: www.ethiometrology.gov.et

Telegram: https://t.me/Ethiopian_Metrology_Institute 

YouTube: https://www.youtube.com/@EthioMetrology