themes/custom/conbiz News | EMI Skip to main content

"የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ" በሚል መሪ ቃል የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ተካሄደ፡፡

ነሐሴ 17-2016 ዓ.ም ኢስኢ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮችና ሠራተኞች "የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ" በሚል መሪ ቃል በዛሬው ዕለት እንጦጦ ፓርክ አካባቢ በመገኘት አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል፡፡

17ኛውን የአፍሪካ አህጉር የሥነ-ልክ ተቋም ስብሰባ የሚካፈል ልዑክ ወደ ኬንያ ማምራቱ ተገለፀ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22/2016 ዓ.ም (ኢስኢ) 17ኛውን የአፍሪካ አህጉር የሥነ-ልክ ተቋም ስብሰባ ለመካፈል በኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፍቅረዓብ ማርቆስ የተመራ ልዑክ በዛሬው እለት ከአቻ የሥነ-ልክ ተቋም አመራሮች እና ቴክኒካል ኮሚቴዎች ጋር በጋራ እና በአህጉር አቀፍ የሥነ-ልክ ጉዳዮች ላይ በናይሮቢ ኬንያ ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛል።

የኢንስቲትዩቱ አመራሮችና ሠራተኞች በ2017 በጀት ዕቅድ እና በጊዜ አጠቃቀም ዙሪያ ውይይት አካሄዱ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24/2016 ዓ.ም (ኢስኢ) የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት አመራሮችና ሠራተኞች በ2017 በጀት ዕቅድ፣ በጊዜ አጠቃቀም፣ መልካም ሥነ-ምግባር እና ለጥናትና ምርምር የተቋሙን ነባራዊ ሁኔታ በማስመልከት በአዳማ ከተማ ውይይት አድርገዋል፤የአዳማ ጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪንም ጉብኝተዋል፡፡

የሀገር ውስጥ የህክምና ግብዓት ምርትና የኢኖቬሽን አውደ ርዕይ በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ነው፡፡

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20/2016 ዓ.ም (ኢስኢ) የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ከአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት እና ከሀገር ውስጥ የህክምና ግብዓት አምራች ማህበራት ጋር በመተባበር ከሰኔ 15-20/2016 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ አውደርዕይ በሚሊኒየም አዳራሽ እያካሄደ ይገኛል፡፡

ኢንስቲትዩቱ “ለተሻለ ነገ ዛሬ እንለካለን” በሚል መሪ ቃል ዓለም አቀፉን የሥነ-ልክ ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች አከበረ፡፡

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2016 ዓ.ም (ኢስኢ) የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት አመራሮችና ሠራተኞች ዓለም አቀፉን የሥነ-ልክ ቀን “ለተሻለ ነገ ዛሬ እንለካለን” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ዝግጅቶች አክብረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት ሠራተኞች የዘጠኝ ወር የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ አካሄዱ፡፡

የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት አመራሮችና ሠራተኞች የተቋሙን የ2016 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወር የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ አካሂደዋል፡፡