themes/custom/conbiz News | EMI Skip to main content

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ ዛሬ ብሔራዊ የጥራት መንደርን መረቁ::

ህዳር 14/2017 ዓ.ም - ኢ.ስ.ኢ በአፍሪከ ደረጃ በአይነቱና በሚሰጠው አገልግሎት ልዩ የሆነና የተለያዩ የጥራት መሠረተ ልማቶችን አንድ አካቶ የያዘው ብሔራዊጥራት በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በይፋ ተመርቋል።

የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት አነስተኛ ገቢ ላላቸው ሠራተኞች የበዓል ስጦታ አበረከተ፡፡

አዲስ አበባ ጳጉሜ 4 ቀን 2016 ዓ.ም /ኢስኢ/ የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር በሰጡት አቅጣጫ መሰረት አዲስ ዓመትንና ጳጉሜ 4 "የህብር ቀን" ምክንያት በማድረግ አነስተኛ ገቢ ላላቸው አርባ ለሚሆኑ የተቋሙ ሠራተኞች ለበዓል መዋያ የሚሆን ዘይትና ዱቄት በስጦታ አበርክቷል፡፡

ኢንስቲትዩቱ ለግንባር ቀደም ሠራተኞች የዕውቅናና ሽልማት ሥነ-ስርዓት አካሄደ፡፡

ነሐሴ 21/2016 ዓ.ም /ኢስኢ/ የኢትዮጵያን ይግዙ በሚል መሪ ቃል ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከነሐሴ 19-23/2016 ዓ.ም ያዘጋጀውን የንግድ ሳምንት ምክንያት በማድረግ የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት በ2016 በጀት ዓመት የጎላ አስተዋፅዖ ላበረከቱ ምስጉን ሠራተኞች የዕውቅናና ሽልማት ሥነ-ስርዓት አካሂዷል፡፡

የኢትዮጵያን ምርትና አገልግሎት መግዛት ዕድገትን ለማፋጠን ያግዛል ተባለ፡፡

አዲስ አበባ፡ ነሐሴ 19/2016 ዓ.ም /የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት የኢትዮጵያን ምርትና አገልግሎት መግዛት የውጭ ምንዛሬን ከማዳን ባሻገር የግሉን የንግድ ዘርፍ ያበረታታል፣ የሀገርንም ዕድገት ያፋጥናል ሲሉ "የኢትዮጵያን ይግዙ" በሚል መሪ ቃል በተከፈተው

"የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ" በሚል መሪ ቃል የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ተካሄደ፡፡

ነሐሴ 17-2016 ዓ.ም ኢስኢ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮችና ሠራተኞች "የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ" በሚል መሪ ቃል በዛሬው ዕለት እንጦጦ ፓርክ አካባቢ በመገኘት አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል፡፡

17ኛውን የአፍሪካ አህጉር የሥነ-ልክ ተቋም ስብሰባ የሚካፈል ልዑክ ወደ ኬንያ ማምራቱ ተገለፀ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22/2016 ዓ.ም (ኢስኢ) 17ኛውን የአፍሪካ አህጉር የሥነ-ልክ ተቋም ስብሰባ ለመካፈል በኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፍቅረዓብ ማርቆስ የተመራ ልዑክ በዛሬው እለት ከአቻ የሥነ-ልክ ተቋም አመራሮች እና ቴክኒካል ኮሚቴዎች ጋር በጋራ እና በአህጉር አቀፍ የሥነ-ልክ ጉዳዮች ላይ በናይሮቢ ኬንያ ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛል።