themes/custom/conbiz በብሔራዊ ጥቅምና ጂኦስትራቴጂያዊ ቁመና ዙሪያ ውይይት ተካሄደ፡፡ | EMI Skip to main content
emi

በብሔራዊ ጥቅምና ጂኦስትራቴጂያዊ ቁመና ዙሪያ ውይይት ተካሄደ፡፡

አዲስ አበባ፡ ጥቅምት 06/2018 ዓ.ም (ኢሥኢ)

የኢትጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት የስራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በብሔራዊ ጥቅምና ጂኦስትራቴጂያዊ ቁመና ዙሪያ ለመንግስት ሠራተኞች በተዘጋጀው ሰነድ ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡

የውይይት ሰነዱን ያቀረቡት የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፍቅረአብ ማርቆስ ሲሆኑ በብሔራዊ ጥቅምና ጂኦስትራቴጂያዊ ምንነት፣ በብሔራዊ ጥቅም መሰረታዊ ግቦች፣ በኢትዮጵያ ጂኦስትራቴጂያዊ ሁኔታና ብሔራዊ ጥቅም፣ በብሔራዊ ጥቅማችን ዋነኛ ፈተናዎች፣ ቁመናዋን ያሳጣት መልከዓምድራዊ እስረኝነት፣ ፈተናዎቹ በብሔራዊ ጥቅማችን ላይ ያሳደሩት ተፅእኖ፣ ብሔራዊ ጥቅምን የሚያረጋግጥ የዲፕሎማሲ አቅም መገንባትና በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችና መሰል ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርገው ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሙሉጌታ ደርበው በበኩላቸው ሰነዱ ከድል ባሻገር ወደፊት የሚጠብቀንን ታላቅ ስራና ሀገራዊ ኃላፊነት በግልፅ የሚያሳይ ነው፡፡ የማይታሰበውንና በብዙ ሴራ ተተብትቦ የነበረውን የህዳሴ ግድብ ማጠናቀቅ የተቻለው ውስጣችንን ሲበላን የኖረውን ቁጭት ወደ ተግባር መቀየር በመቻላችን መሆኑን መገንዘብ ይኖርብናል ብለዋል፡፡

እንደ ህዳሴው ግድብ ሁሉ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄያችን ትክክለኛና ፍትሃዊ በመሆኑ ያሉትን የሠላም አማራጮችና ዲፕሎማሲ ተጠቅመን በቅርብ ጊዜ እንደምናሳካው ሙሉ እምነት አለኝ ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ እኛ የመንግስት ሠራተኞችም የተጣለብንን ህዝብን የማገልገል ኃላፊነት በታማኝነትና በትጋት በመወጣት ተቋማችንን መገንበት በሌላ በኩል ደግሞ የሀገርን ርዕይ ማሳካት ይጠበቅብናል ሲሉ አጽንኦት ሰጥተው አስገንዝበዋል፡፡

በመጨራሻም በቀረበው ሠነድ ላይ ከተሳታፊዎች በርካታ ሀሳቦች የተንሸራሰሩ ሲሆን የተጋረጡብንን ችግሮችና የተቀነባበሩ ውስብስብ ሴራዎችን በጥበብና በአንድነት በመታገል የባህር በር ጥያቄያችንን እውን እናደርጋለን፤ ተግተን ለመስራትና ውጤት ለማስመዝገብ የዜግነት ድርሻችንንም ለመወጣት ተዘጋጅተናል ሲሉ አስረድተዋል፡፡