በበጀት ዝግጅትና አስተዳደር መመሪያ ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ፡፡
ስልጠናውን የሰጡት በኢፌዴሪ ገንዘብ ሚኒስቴር የኢኮኖሚ በጀት ዲቪዥን ኃላፊ አቶ ዳዊት ብርሃኑ ሲሆኑ የበጀት ዝግጅትና አስተዳደር መመሪያን አስመልክተው ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በሌላ በኩል የኢንስቲትዩቱ የዕቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ስንታየሁ ወንድሙ በሰጡት ማጠቃለያ እንደተናገሩት ይህ ስልጠና በቀጣይ ለምናዘጋጀው የ2017 እና 2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ግብዓት የተገኘበት፤አዲስ ለሆኑ የስራ ክፍል ኃላፊዎች ደግሞ ግንዛቤ የተፈጠረበት መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ዳይሬክተሯ አያይዘውም የተሰጠውን ስልጠና መሰረት በማድረግ የተቋሙ የስራ ክፍሎች የተሟላ ዕቅድ እንደሚያዘጋጁ ያላቸውን እምነት ገልፀው ገንዘብ ሚኒስቴር ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት በፈለግነው ጊዜ የስራ ኃላፊ በመላክ ስልጠናውን እንድንወስድ ስለረዳን ምሥጋና አቀርባለሁ ብለዋል፡፡