19ኛው የብሔራዊ ሠንደቅ ዓላማ ቀን በጥራት መንደር ተከበረ፡፡
19ኛው የብሔራዊ ሠንደቅ ዓላማ ቀን በጥራት መንደር ተከበረ፡፡
አዲስ አበባ፡ ጥቅምት 02 ቀን 2019 ዓ.ም… ኢሥኢ
የኢትየጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩትን ጨምሮ የጥራት መንደር አመራሮችና ሠራተኞች በጋራ “ሠንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን” በሚል መሪ ሀሳብ 19ኛውን የብሔራዊ ሠንደቅ ዓላማ ቀን አክብረዋል፡፡
በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር መዓዛ አበራ እንደገለፁት እንደ ሀገር 7ኛውን ዙር ሀገራዊ ምርጫ ባሸነፍንበትና አዲስ የመንግስት ምስረታ በተካሄደበት ማግስት ቀኑ መከበሩ በዓሉን ልዩ ያደርገዋል፡፡ ሠንደቅ ዓላማ መስቀል ብቻ ሳይሆን ለህዝባችን በታማኝነት፣ በቅንንት፣ በፍፁም ክብር የምናገለግልበትና ዳግም ቃል የምንገባበት ጊዜ ነው ብለዋል፡፡
ዋና ዳይሬክተሯ አክለውም መንግስት በ2050 የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመፍጠር የያዘውን ዕቅድ ለማሳካት ሁሉም አመራርና ሠራተኛ የሀገርን ክብር ከፊት በማስቀደም ጌዜውን፣ እውቀቱንና ያለውን አቅም ሁሉ ማበርከትና በጋራ መረባረብ ወቅቱ የሚጠይቀው ሀገራዊ ግዴታ ነው ሲሉ በአፅንኦት አስገንዝበዋል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ
Facebook: http://www.facebook.com/emi.ethiopia
Website: www.ethiometrology.gov.et
Telegram: https://t.me/Ethiopian_Metrology_Institute
YouTube: https://www.youtube.com/@EthioMetrology
Email: info@ethiometrology.gov.et